የአካውንቴን አንዳንድ የግል መረጃ መቀየር/ማስተካከል ብፈልግስ?

የግል መረጃዎን ማስተካከል ቢፈልጉ በመጀመሪያ ወደ ጃሚፔይ አካውንቶ ይግቡ፤ በመቀጠልም ‘ማህበሮች’ በሚለው ስክሪን ገፅ የቀኝ ግርጌ ላይ ‘የግል መረጃ’ ሚለውን በመጫን ይምረጡ፤ ይህም ‘ስለ እርሶ’ ወደ ሚል ገፅ ይወስዶታል። በገፁ ላይ የሚገኙትን ‘መረጃ ቀይር’ የሚሉ መደቦች ስም፣ ፆታ፣ ቋንቋ፣ ስልክ ቁጥር፣ ዙር ቁጥር የመሳሰሉትን መረጃዎች መቀየር ይቻላሉ። በተጨማሪም በገፁ አናት ላይ ‘ስለ እርሶ’ ከሚለው ፅሁፍ ስር በሚገኝው ክብ ምልክት ውስጥ ያለውን የካሜራ ምልክት በመጫን ምስሎን/ፎቶግራፎን መቀየር ይችላሉ።