‘የማህበር ባለቤት’፣ ‘ወኪል’ እና ‘አባል’ በሚሉት የስራ ድርሻዎች መካከል ያለው ልዩነት ምንድነው?

ማህበር ባለቤት ለቁጠባ ማህበሩ የጃሚፔይ አካውንት የከፍተው ሰው የማህበር ባለቤት ይሆናል። አንድ የማህበር ባለቤት ወኪል ካልሆነ በስተቀር የማህበሩን መረጃ መመዝገብም ሆነ መቀየር አይችልም።

ወኪል አንድ ወኪል በመተግበሪያው ውስጥ የሚመዘገበውን መረጃ ሁሉ የመመዝገብ እና የማረም መብት አለው። በቡድኑ ስምምነት እና በተወካዩ ፈቃደኝነት መሰረት ወኪሉ የማህበሩ አባል ወይም የመንደሩ ወኪል (village agent) ወይም የNGO ሰራተኛ ሊሆን ይችላል። አንድ ማህበር ከአንድ በላይ ወኪል ሊኖረው ይችላል።

አባል በቁጠባ ማህበሩ ውስጥ መደበኛ የቡድኑ አባል ሲሆን በመተግበሪያው ውስጥ የሚመዘገበውን መረጃ የመመዝገብም ሆነ የማረም መብት የለውም። ነገር ግን የተመዘገበውን ሁሉ ማየት እና መከታተል ይችላል።