በተለያየ ምክንያት አንድ አባል ዙሩ ከማለቁ በፊት የቆጠቡትን እጣ መውሰድ ቢፈልጉ እና የቡድኑ አባላት መክረው ከተስማሙበት ወጪ እጣዎቹን በቀላሉ መመዝገብ ይቻላል። ይህንን ለማድረግ የስብሰባው ዝርዝር መገለጫ ገፅ ላይ በመሄድ ከስክሪኑ በስተቀኝ ግርጌ ያለውን ክብ ሰማያዊ ምልክት በመጫን ከሚመጡልን አማራጮች ‘የአባል ወጪ እጣ’ የሚለውን እንመርጣለን። በመቀጠልም ከስም ዝርዝር ውስጥ የአባሉን ስም በመምረጥ ወጪ እጣውን መመዝገብ ይቻላል። እጣ ወጪ ሲያደርጉ ምክንያቱንም አብረው መመዝገብ ይኖርብዎታል።