ሳጥኑ ውስጥ ያለው ብር አፑ ከሚያሳየው መጠን ጋር ልዩነት ካለውስ?

በስብሰባው መጨረሻ ላይ አፑ የሚያሳየው የብር መጠን መዝገቡ ከሚያሳየው የብር መጠን ከተለየ እንደገና ተመልሰው የተመዘግቡትን እጣዎች፥ብድሮች እንዲሁም ቅጣቶች ትክክል መሆናቸውን እና የድምር ስህተት አለመኖሩን ያረጋገጡ። አፑ በተመዘገበው መሰረት ስለሆነ ሂሳብ የሚሰራው የተመዘገቡት ቁጥሮች ትክክል ከሆኑ አይሳሳትም።