አንድ አባል ከአምስት በላይ እጣ በአንድ ስብሰባ ላይ ቢገዛስ?

የburger tab icon blue ምስል ውጤት

አንድ አባል በተለያዩ ምክንያቶች ከአምስት በላይ እጣ በአንድ ስብሰባ ላይ ቢገዛ እና የቡድኑ አባላት መክረው ከተስማሙበት ይህንን እንደሚከተለው መመዝገብ ይቻላል። በመጀመሪያ የስብሰባው ዝርዝር መገለጫ ገፅ ላይ በመሄድ ከስክሪኑ በስተቀኝ ግርጌ ያለውን ክብ ሰማያዊ ምልክት  በመጫን ከሚመጡልን አማራጮች ‘የአባሉ ገቢ እጣ’ የሚለውን እንመርጣለን። ቀጥሎ በሚመጣልን ገፅ ላይ አባሉን በመምረጥ የእጣዎቹን መጠን እንመዘግባለን። ይህን በምናደርግባት ግዜ የገቢ እጣ ምክንያቱንም አብረን መመዝገብ ይኖርብናል።