አንድ አባል ማህበሩን መልቀቅ ቢፈልጉስ?

በተለያየ ምክንያት አንድ አባል ከማህበሩ መልቀቅ ቢፈልጉ እና የቡድኑ አባላት መክረው ከተስማሙበት አባሉ ከማህበሩ መልቀቃቸውን መመዝገብ ይቻላል። ይህንን ለማድረግ በመጀመሪያ ‘ማህበሮች’ በሚለው ስክሪን ገፅ ላይ የማህበሮን ስም በመጫን ይምረጡ፤ በመቀጠልም ‘አባላት’ የሚለውን በመጫን  ከስም ዝርዝር ውስጥ የሚለቁትን አባሉ ስም እንመርጣልን። ይህም ‘የአባል መታወቂያ’ ወድ ሚል ገፅ ይወስዳል። በገፁ ወጨረሻ ላይ ‘ተጠቃሚውን አስውጣ’ የሚለውን ስማያዊ መደብ በመጫን መመዝገብ ይችላሉ። ይህን ሲመዘግቡ አባሉ ከማህበሩ የለቀቁበትን ምክንያት አብረው መመዝገብ ይኖርብዎታል።

ጥቆማ:

ይህንን ከማድረጎ በፊት ግን አባሉ በዙሩ የቆጠቡትን እጣ በሙሉ መውሰድ ይኖርባቸዋል። ይህንን ለማድረግ የስብሰባው ዝርዝር መገለጫ ገፅ ላይ በመሄድ ከስክሪኑ በስተቀኝ ግርጌ ያለውን ክብ ሰማያዊ ምልክት በመጫን ‘የአባል ወጪ እጣ’ የሚለውን እንመርጣለን። በመቀጠልም ከስም ዝርዝር ውስጥ የአባሉን ስም በመምረጥ ወጪ እጣውን መመዝገብ ይቻላል። እጣ ወጪ ሲያደርጉ ምክንያቱንም አብረው መመዝገብ ይኖርብዎታል።