ቡድኑ ለተለያዩ ነገሮች ወጭ ካወጣ እና የቡድኑ አባላት መክረው ከተስማሙበት የቡድኑን ወጪ በቀላሉ መመዝገብ ይቻላል። ይህንን ለማድረግ የስብሰባው ዝርዝር መገለጫ ገፅ ላይ በመሄድ ከስክሪኑ በስተቀኝ ግርጌ ያለውን ክብ ሰማያዊ ምልክት በመጫን ከሚመጡልን አማራጮች ‘የቡድኑ ወጪ’ የሚለውን እንመርጣለን። ቀጥሎ በሚመጣልን ገፅ ላይ የወጪውን ዝርዝር እንመዘግባለን። ይህን በምናደርግባት ግዜ የገቢ እጣ ምክንያቱንም አብረን መመዝገብ ይኖርብናል።