የቁጠባ ማህበሩን አንዳንድ መረጃ መቀየር/ማስተካከል ቢያስፈልግስ? (ለምሳሌ አዲስ ዙር ሲጀመር)

የቁጠባ ማህበሮን መረጃ ማስተካከል ቢያስፈልግ በመጀመሪያ ‘ማህበሮች’ በሚለው ስክሪን ገፅ ላይ የማህበሮን ስም በመጫን ይምረጡ፤ በመቀጠልም በገፁ አናት ላይ ‘ሳጥን ውስጥ ያለው ብር’ ከሚለው ፅሁፍ በላይ በሚገኝው ክብ ምልክት ውስጥ ያለውን አነስተኛ ክብ ይጫኑ፤ ይህም ‘የቡድኑ መረጃ’ ወደ ሚል ገፅ ይወስዶታል። በገፁ ላይ የሚገኙትን ‘መረጃ ቀይር’ የሚሉ መደቦች በመጫን የማህበሩን ስም፣ ዙር ቁጥር፣ የአግልግሎት ክፍያ፣ የአንድ እጣ ዋጋ የመሳሰሉትን መረጃዎች መቀየር ይቻላል። በተጨማሪም በገፁ አናት ላይ ‘የቡድኑ መረጃ’ ከሚለው ፅሁፍ ስር በሚገኝው ክብ ምልክት ውስጥ ያለውን የካሜራ ምልክት በመጫን የማህበሩን ምስል/ፎቶግራፍ መቀየር ይችላሉ።