የግልዎን ወይም የማህበሮን ምስል/የመለያ ፎቶግራፎ መቀየር ከፈለጉስ?

የግልዎን ምስል/የመለያ ፎቶግራፎ ለመቀየር

በመጀመሪያ ወደ ጃሚፔይ አካውንቶ ይግቡ፤ በመቀጠልም ‘ማህበሮች’ በሚለው ስክሪን ገፅ የቀኝ ግርጌ ላይ ‘የግል መረጃ’ ሚለውን በመጫን ይምረጡ፤ ይህም ‘ስለ እርሶ’ ወደ ሚል ገፅ ይወስዶታል። በገፁ አናት ላይ ‘ስለ እርሶ’ ከሚለው ፅሁፍ ስር በሚገኝው ክብ ምልክት ውስጥ ያለውን የካሜራ ምልክት በመጫን ምስሎን/ፎቶግራፎን መቀየር ይችላሉ።

የማህበሮን ምስል/የመለያ ፎቶግራፎ ለመቀየር

በመጀመሪያ ‘ማህበሮች’ በሚለው ስክሪን ገፅ ላይ የማህበሮን ስም በመጫን ይምረጡ፤ በመቀጠልም በገፁ አናት ላይ ‘ሳጥን ውስጥ ያለው ብር’ ከሚለው ፅሁፍ በላይ በሚገኝው ክብ ምልክት ውስጥ ያለውን አነስተኛ ክብ ይጫኑ፤ ይህም ‘የቡድኑ መረጃ’ ወደ ሚል ገፅ ይወስዶታል።